
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን እና አዲሱን የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን በይፋ መርቀዋል። እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ፤ የአካባቢውን እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እና ቱሪዝምን የማሳደግ ርዕይን ሰንቆ በሳምንት ሦስት በረራዎችን ያስተናግዳል ነው ያሉት። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያነቃቃል፣ እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ሲሉ አብራርተዋል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዳችን በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
#አሚኮ #ethiopianairlines #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
