በዓሉን በጋራ ማዕድ በመጋራት ማሳለፍ ይገባል።

4

 

ፍኖተ ሰላም: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በፍኖተ ሰላም ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ምክትል ሠብሣቢ ሐጂ ሀሰን አሊ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እና ለከተማዋ ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሐጂ ሀሰን ዒድ ደስታ ነው ብለዋል። በዓሉ በሰላም እና በደስታ እየተከበረ መኾኑንም አስታውቀዋል።

ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸውን እስማኤልን ለመስዋዕትነት ሊያቀርቡ ሲሉ ከአሏህ ዘንድ በግ መውረዱን በማስታወስ በእርድ የሚከበር በዓል መኾኑንም ተናግረዋል።

በዓሉን ከምስኪኖች፣ ከችግረኞች፣ ከቤተሰብ እና ከጎረቤት ጋር ማዕድ በመጋራት ማሳለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ወርቁ በላይ ፤ ስለ ከተማዋ እና ስለ ሀገሪቱ ሰላም በመነጋገር፣ በመመካከር እና አዎንታዊ አስተዋጽኦ በማበርከት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ከተማዋ በአሁኑ ወቅት ለምትገኝበት አንጻራዊ ሰላም የሃይማኖቱ ተከታዮች ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከከተማው አስተዳደር ጎን በመሰለፍ በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #ዒድ_አልአደሃ #አረፋ_በዓል #ፍኖተሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሀረር ከተማ እየተከበረ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የነጌሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን መረቁ።