የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሀረር ከተማ እየተከበረ ነው።

2

 

ባሕር ዳር፡ በሀረሪ ክልል 1ሺሕ 447ኛው የዒድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሀረር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በክልሉ በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኙ የሃይማኖቱ ተከታዮች ከማለዳው ጀምሮ በሀረር በሚገኘው ኢማም አሕመድ ስታድየም በመሰባሰብ እያከበሩት ይገኛሉ።

በበዓሉ አከባበር ላይም የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

#አሚኮ #ሐረር #ኢድአልአደሃ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🕋 “የፅድቋ ከተማ መካ”
Next articleበዓሉን በጋራ ማዕድ በመጋራት ማሳለፍ ይገባል።