
ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ ለማስጀመር ደሴ ከተማ ገብተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደሴ ከተማ አሥተዳደር ተገንብተው የተጠናቀቁ የልማት ሥራዎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ሥራዎችንም እንደሚጎበኙ እና የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#አሚኮ_ዜና #የልማት_ሥራ #ደሴ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
