“የብልጽግና የጠራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀርፆ የልማት ሥራዎችን ሠርቷል” አቶ አየን ብርሃን

1
እንጂባራ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ አየን ብርሃን ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ ዕኩልነት፣ ሰላም እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲሰፍን የሚሠራ፣ የጠራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀርፆ ሰፊ የልማት ሥራዎችንም የሠራ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት በኮሪደር ልማት፣ በግብርና እና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያስመዘገባቸው ስኬቶች አቅዶ መፈፀም የሚችል ፓርቲ መኾኑን በተግባር ያረጋገጠበት ነው ብለዋል።
አቶ አየን ሕዝቡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በነጻነት ቆሞ እና ለሚበጀውን ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ አይተነው ታዴ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሥልጣን መያዝ የሚቻለው በምርጫ ካርድ ብቻ መኾኑን ገልጸዋል።
የእንጅባራ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
ሕዝቡ ልማትን ለማስቀጠል ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን እንዲሠራም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ በቃሉ ፈረደ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ብልጽግና በተቋማዊ እና ሕዝባዊ ባሕል ላይ በመቆም ኢትዮጵያን ለመገንባት ጠንክሮ የሚሠራ ፓርቲ ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ