🕌 “ኢድ አል አደሃ (አረፋ) የመታዘዝ እና የመተሳሰብ ታላቅ መድረክ”

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት እና መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አንዱ ነው።

በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን የሼሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ ሼህ ወላላው ሰዒድ የኢድ አል አደሃ በዓል በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።

​የበዓሉ ዋነኛ መገለጫ ማኅበራዊ መተሳሰብ መኾኑን የገለጹት ሼህ ወለላው አማኙ ለፈጣሪው ያለውን ፍጹም መታዘዝ ከሰው ልጆች ጋር በፍቅር እና በሰላም ከመኖር ጋር ያስተሳሰረ መኾኑን አስረድተዋል።
​
​ሼሪዓው እና ነብዩ ሱና ባዘዘው መሠረት ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የእርድ ሥጋውን ለሦስት እኩል ከፍሎ ማካፈል እንዳለበት ተደንግጓል ነው ያሉት። በዚህም መሠረት፦

👉 አንድ ሦስተኛው (ሲሶው) አቅም ለሌላቸው ይሰጣል።
👉 አንድ ሦስተኛው ለጎረቤት እና ለማኅበረሰቡ በጋራ መዋያ ይውላል፤
👉 የቀረው አንድ ሦስተኛው ደግሞ ለቤተሰብ ፍጆታ እንዲኾን ይደረጋል ነው ያሉት።

​ይህ ሥርዓት ኢድ አል-አደሃ በዓል አማኙ ደስታውን ከሌሎች ጋር እንዲጋራ ያደርገዋል ብለዋል።

በመስጠት ውስጥ የሚገኘው በረከትም አማኙ ከአላህ ዘንድ የሚያገኘውን መንፈሳዊ ምንዳ ወይም አጅር ይጨምረዋል፤ በሰጪው እና በተቀባዩ መካከል ያለውን ፍቅር እና የልብ ትስስርም ያጠናክራል ነው ያሉት።

ኢድ አል አድሃ እና መተሳሰብ የማይነጣጠሉ እሴቶች ናቸው ያሉት ሼህ ወለላው ይህ ማኅበራዊ ትስስር ከሃይማኖቱ ተከታዮች ባለፈ ከሌላው ማኅበረሰብ ጋርም ደስታችሁ ደስታችን ነው በሚል በጋራ አብሮ የመኖርን ባሕል ይበልጥ እንደሚያጎለብተው አስገንዝበዋል።

​ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የልማት ሥራዎችን ለመመረቅ ደሴ ገቡ።
Next article🕋ሃጅ እና ሃይማኖታዊ በረከቶቹ