
ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ እና የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች በጋራ በመኾን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አማካሪ ግዛቸው ሙሉነህ ብልጽግና ፓርቲ ቃሉን በተግባር እየፈጸመ ያለ ድርጅት መኾኑን ገልጸዋል። ከለውጡ ማግሥት በኋላ በርካታ የሕዝብ መሠረተ ልማቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማከናወን የቻለ ፓርቲ መኾኑንም አስገንዝበዋል።
የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃየሁ አስረስ ብልጽግና ፓርቲ ከነጠላ ትርክቶች ይልቅ አካታችነትን ያስቀደመ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ሰው ተኮር እና በሃሳብ ልዕልና የሚያምን አቃፊ ፓርቲ መኾኑን ጠቁመዋል።
የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ደሳለው አምሳል ፓርቲው በወል ትርክት ግንባታ ትልቅ ሚና እየተወጣ መኾኑን አብራርተዋል።
ኅብረ ብሔራዊነትን እና አብሮነትን ማጎልበት፣ ገለልተኛ የመንግሥት ተቋማትን መገንባት እና ብሔራዊ መግባባትን ማምጣት የፓርቲው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መኾናቸውንም አስረድተዋል።
በዕለቱ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከልም፦
👉 በአብሮነት እንቆማለን፣ በብልጽግና እንሻገራለን፤ ሰላማችን ለብልጽግናችን መሠረት ነው፤
👉በዘመናዊ ግብርና የምግብ ዋስትናን እናረጋግጣለን፤
👉ወጣቶች የለውጥ ሞተር፣ የብልጽግና ግንባር ቀደም ኀይል ናቸው የሚሉ እና ሌሎችም ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምን እና ልማትን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ #አዊ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
