
ጎንደር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ ነው። ግንባታው የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተሠሩለት መኾኑ ተመላክቷል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ግንባታው በጥራት እየተገነባ መኾኑን ገልጸዋል። በአጭር ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲኾንም አሳስበዋል።
በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
#አሚኮ_ዜና #መሶብ_የአንድማዕከል አገልግሎት #ጎንደር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
