
ደሴ: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን የአልብኮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል።
የአልብኮ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አብደላ ሰይድ የወረዳው ማኅበረሰብ ለሰላም፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲ ዕድገት የዳበረ ልምድ ያለው ሕዝብ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ እና በብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት እጩ ደምስ እንድሪስ “ብልጽግና የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎችን በመመከት የሀገርን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን እየተለመ እና እየፈጸመ ነው” ብለዋል።
በወረዳው የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ቃል በመግባት ብቻ ሳይኾን በተግባር እየመለሰ መኾኑንም ገልጸዋል።
ለአሚኮ አስተያየታቸውን የሰጡ የወረዳው ነዋሪዎች ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ እንዲኾን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
