“ሕዝባችን የአብሮነት እና የመቻቻል መገለጫ ነው” አቶ አህመድ አሊ

5

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አሥተዳደር አርጡማ ፉርሲ ወረዳ እና በጨፋ ሮቢት ከተማ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ማሻገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በዚሁ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አባገዳዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ ሕዝባችን የአብሮነት እና የመቻቻል መገለጫ ነው ብለዋል።

ሕዝብ የሚጠቅመውን ሲረዳ በራሱ ተነሳሽነት ድጋፉን ይገልጻል ነው ያሉት። ሕዝቡ ሀገሪቱ ገጥሟት የነበረውን የፖለቲካ ስብራት ለመለወጥ በቁርጠኝነት ተንቀሳቅሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ያመጣ መኾኑን ጠቅሰዋል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጀማል አሊ ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት በተግባር የሚገለጽበት ዋና መሣሪያ መኾኑን ገልጸዋል።

“መጭው ጊዜ ምርጫችንን በድምጽ ካርዳችን ብቻ የምንወስንበት ይኾናል” ያሉት አቶ ጀማል የዴሞክራሲ ሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ለታገለው ሕዝብ እና ለመሪዎች ምሥጋና አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ 🗳 #ኦሮሞ_ብሔረሰብ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥነው የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ።
Next article“ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ እንዲኾን የድርሻችንን እንወጣለን” የአልብኮ ወረዳ ነዋሪዎች