በደሴ ዙሪያ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ትውውቅና የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ።

3

 

ደሴ፡ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ዙሪያ ወረዳ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን የማስተዋወቅ እና የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው የተጀመረውን ሰላም እና ልማትን የማረጋገጥ ልዕልና ለማሳካት ፓርቲው በቁርጠኝነት እየሠራ እንደኾነ ገልጸዋል።

በፓርቲው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት በአማራ ክልል ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ከሚቴ ሠብሣቢ ሀናን አብዱ ለወረዳው ዕድገት እና ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ስለመኾናቸው ተናግረዋል።

በፓርቲው የደሴ ዙሪያ ወረዳን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወከል የሚወዳደሩት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ጀማል ሙሐመድ ​በወረዳው ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሕዝቡ ድምጽ ወሳኝ መኾኑንም ነው የተናገሩት።

አሚኮ ያነጋገራቸው የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች በወረዳው በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ እንደኾነ አንስተዋል።

በምዝገባ ወቅት በንቃት መሳተፋቸውን ያስታወሱት ነዋሪዎች በምርጫው ዕለትም ለሀገር ሰላም እና ዕድገት እንዲሁም ለሕዝብ ተጠቃሚነት ይሠራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋዬ

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ #ደሴ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር ከተማን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታን ጎበኙ።
Next articleበመተማ ዮሐንስ ከተማ ባለሦሥት ወለል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።