ኢንዱስትሪ ፓርኩ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሰላምን መጠበቅ ይገባል” አቶ መላኩ አለበል

7

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን ግንባታ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ፓርኩ ከበለሳ እስከ ሻውራ፤ ከቋራ እስከ ፎገራ ድረስ ያለውን አካባቢ የግብርና አቅም የሚጠቀም ትልቅ ፕሮጀክት መኾኑን ተናግረዋል።

የጎንደር አካባቢ የግብርና ምርቶችን ለማቀነባበር ለግብዓት የተመቸ መኾኑንም ገልጸዋል። ለግብርና ምርቶች ገቢ የሚያስገኝ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር እና ከተሞችን የሚያሳድግ መኾኑን ነው የተናገሩት።

ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ፓርኩ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሰላምን መጠበቅ እንደሚገባ አንስተዋል። ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ልማት እንዲፋጠንም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ከግንባታው ጎን ለጎን ባለሀብቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል። በቁርጠኝነት የሚያለሙ ባለሃብቶችን ከወዲሁ መመልመል እንደሚገባም ነው የገለጹት።

አርሶ አደሮችም ምርታቸውን ማሳደግ አለባቸው ብለዋል። የክልሉ መንግሥት ይህ ፕሮጀክት እንዲጀመር ስላደረገ ምስጋና አቅርበዋል።

የጥናት ሥራውን ለሠራው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና መሬታቸውን በፈቃደኝነት ለሰጡ የአካባቢው አርሶ አደሮችም ምስጋና ችረዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ኢንዱስትሪ ፓርኩ የቀጣናው የኢኮኖሚ ስበት ማዕከል ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleየኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥነው የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ።