
ፍኖተ ሰላም: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወንበርማ ወረዳ እና የሽንዲ ከተማ ነዋሪዎች በጋራ በመኾን ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል።
የወንበርማ ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ አብዩ ጌቴው ብልጽግና ፓርቲ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበ እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየተጋ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ፓርቲው ፈተናዎችን ወደ ድል እየቀየረ ያለ መኾኑንም ተናግረዋል። በምርጫው ሂደት ሁሉም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ዓለሙ ፓርቲው የመግባባት ዴሞክራሲን በተሟላ መንገድ ለመፍጠር እየሠራ ነው ብለዋል።
ምርጫው የተጀመሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ወሳኝነት እንዳለውም ነው የገለጹት።
የአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ በትግሉ ተስፋሁን ምርጫው ታሪካዊ ጠላቶች ሀገርን ለማተራመስ እየሞከሩ ባሉበት ወቅት መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ምርጫን ማካሄድ ሰላምን እና ልማትን ማጽናት እንደኾነም አስረድተዋል።
#አሚኮ #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ሀገር
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
