“ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገዋል።

የመካነ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ፍቅርተ ካሳው ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራትን በስኬት ማጠናቀቁን ተናግረዋል።

ቀጥተኛ የንግድ ትሥሥርን ለመፍጠር እና ሴቶችን ይበልጥ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ብልጽግና በቀጣይም በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።

በከተማ አሥተዳደሩ የኮሪደር ልማት፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ልማት እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች እንዲስፋፉም ይሠራል ብለዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ልማቶች እንዲሳለጡ እና የሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲ ትኩረት ሰጥቶ ሢሠራ መቆየቱን አንስተዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ብልጽግና የሕዳሴ ግድብን፣ ገበታ ለሀገርን፣ ገበታ ለትውልድን እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመፈጸም ዕድሎችን መፍጠር የቻለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የሕዝብን ጥቅም ማረጋገጡንም አንስተዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ብልጽግና ፓርቲ ለነገዋ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት እየሠራ ነው ብለዋል።

ብልጽግና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ እንደኾነም ገልጸዋል።

አርሶ አደሮች የሀገር መሠረት ናቸው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ የአርሶ አደሮችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፓርቲው በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

#አሚኮ #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ሀገር

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ለቀጣዩ ትውልድ የምትበጅ ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next articleምርጫን ማካሄድ ሰላምን እና ልማትን ማጽናት ነው።