“ለቀጣዩ ትውልድ የምትበጅ ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

10

 

ደብረብርሃን: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን ቡልጋ ከተማ አሥተዳደር “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ማሻገር” በሚል መሪ መልዕክት የፓርቲው ከፍተኛ መሪዎች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል።

በቅስቀሳው ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በዲፕሎማሲ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን አብራርተዋል። ዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።

ዶክተር አሕመዲን ፓርቲው ለኢንዱስትሪ የተመቸች፣ ሰላማዊ እና ለቀጣዩ ትውልድ የምትበጅ ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ የፓርቲው ዋና ትኩረት ሕዝባዊ ጥያቄዎችን መመለስ መኾኑን አንስተው የቡልጋ ከተማ የኢንዱስትሪ መናኸሪያ በመኾኗ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እየፈጠረች እና ባለሀብቶችን እየሳበች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የሕዝቡን የሰላም ባሕል በማጠናከር ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማኅበረሰቡ ኀላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል።

የቡልጋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ውድነህ አየለ ብልጽግና ፓርቲ የልማት ጥያቄዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ በመመለስ ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ መኾኑን አስገንዝበዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ያደሩ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በከፍተኛ ተነሳሽነት እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

በምርጫ ቅስቀሳው ላይ የተገኙ ነዋሪዎችም ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ ምርጫው ስኬታማ ኾኖ እንዲከናወንም የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ ስንታየሁ ኃይሉ

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ሰሜን_ሽዋ #ቡልጋ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን አስጀመሩ።
Next article“ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)