
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፤ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የጎንደር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር የሚያሳልጥ ትልቅ የልማት ፕሮጀክት ነው ተብሏል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#አሚኮ #ጎንደር #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
