ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የልማት ሥራዎችን ለማስጀመር ጎንደር ገቡ።

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የልማት ሥራዎችን ለማስጀመር ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፤ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ጎንደር ገብተዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚገነባውን የኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ ያስጀምራሉ።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብልጽግና የ30 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እቅዶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የገባ ፓርቲ ነው” የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አሊ ይማም
Next article“ምርጫው ነጻ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቀውን ኀላፊነት እንወጣለን” የአርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ