
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀረሪ ክልል በብልፅግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ አፈፃፀም መመዝገቡን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ በፓርቲው መሪነት ባለፉት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ እና በሌሎችም የልማት መስኮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ፓርቲው ወንድማማችነትንና አብሮነትን በማጠናከር እውነተኛ ሕብረ-ብሔራዊነትን በተግባር በማረጋገጥ ቋንቋ እና የጋራ ማንነትን ለኢትዮጵያ ብልፅግና ምሶሶ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን አስገንዝበዋል።
ከልዩነት አንድነትን፣ ካለፈ ጥላቻና ቁርሾ የነገ ተስፋን፣ ትብብርና ኅብረትን መሰረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡንም አብራርተዋል።
በኢኮኖሚ ረገድም በግብርና እና በቱሪዝም ልማት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
በማኅበራዊ ልማት ዘርፍም የትምህርት ጥራት ከማጎልበትና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንጻር የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ኃላፊው እንዳሉት ፓርቲው ለሰው ተኮር ሥራዎች በሰጠው ትኩረት የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ችሏል።
በቀጣይም በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ አበረታች ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል ቀጣይ ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መራጮች ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
