ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

7

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካል እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ የኾነው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል ብለዋል።

ቁልፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መሰል ፋብሪካዎች ግንባታ፣ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በመላ ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተግባር ያረጋገጠ ነው።

‎​ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ መኾኑን ገልጸዋል። ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም ያገኛል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት እና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፣ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ብልጽግና ፓርቲ የላቀ ሃሳብ በማዋጣት ወጣቶችን ይዞ ወደፊት የሚራመድ ፓርቲ ነው።”
Next article🗳️ “ክልሉ መንግሥት አልባ እንዲኾን አንፈልግም፤ ምርጫ ማድረግ መሠረታዊ ነው” የስማዳ ወረዳ ነዋሪዎች