“ብልጽግና ፓርቲ የላቀ ሃሳብ በማዋጣት ወጣቶችን ይዞ ወደፊት የሚራመድ ፓርቲ ነው።”

5

 

ደብረታቦር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተመሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ መልዕክት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ የከተማዋ ወጣቶች ክንፍ አዘጋጅነት የብልጽግና ፓርቲ ቅስቀሳ ተደርጓል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አማካሪ ባየ አለባቸው ፤ ብልጽግና ፓርቲ የላቀ ሃሳብ በማዋጣት ወጣቶችን ይዞ ወደፊት የሚራመድ ፓርቲ እንደኾነም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተመሳሌት ሀገር ለማድረስ የወጣቶች ድምጽ ከሁሉም በላይ እንደኾነም አስረድተዋል።

“ወጣቶች ይመርጣሉ ሀገርን ያፀናሉ” ያሉት አቶ ባየ አለባቸው ምርጫው ነጻ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ግንባር ቀደም መኾን አለባቸው ብለዋል።

“በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት የሕዝብ ሉዓላዊነትን ያረጋግጣል” ያሉት ደግሞ የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ናቸው።

ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ፓርቲ በመኾኑ በልማት እና በምርጫ ሥራዎች ወጣቶች ከፓርቲው ጎን በመሰለፍ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ወጣቶች የምርጫ ካርድ በማውጣት እና በድጋፍ ሰልፍ ያሳዩትን በጎ ተግባር ድምጽ በመስጠት እና ሰላምን በማረጋገጥ እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ #ደብረታቦር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ “ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ በጉጉት እየጠበቅን ነው” የስማዳ ወረዳ ነዋሪዎች