
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት የሴቶች የእግር ጉዞ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል።
የከተማ አሥተዳደሩ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ሰብለ ዘውዱ፤ ብልጽግና ፓርቲ የሴቷን መብት እና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ሴቶችም ይህንን ተገንዝበው ፓርቲውን እየደገፉ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታች የኾነውን ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጡም ጥሪ አቅርበዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የባሕር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ ሰላማዊት ዓለማየሁ የተረጋጋ መንግሥት ለመመሥረት ምርጫ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ሴቶች የእናትነት ጥበባቸውን ለሰላማዊ ምርጫ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስረድተዋል።
ፓርቲው ባለፉት ስምንት ዓመታት የሴቶችን ተሳትፎ፣ ውክልና እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ “ሴቶች ይችላሉ ሀገር ያሻግራሉ” በሚል ሰፊ ሥራ መሥራቱንም ጠቅሰዋል።
ይህ የብልጽግና ፓርቲ ጅማሮ እንዲጠናከር ሴቶች ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ አለባቸውም ነው ያሉት።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የከተማ አሥተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ሴት ደጋፊዎች እያደረጉ ለሚገኙት አስተዋጽኦ አመሥግነዋል።
ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ባሕር_ዳር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
