
ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ንግግር ይበልጥ ውስብስብ እየኾነ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ኢራን የዩራኒየም ክምችቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን በኢራን የዩራኒየም ክምችት ላይ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ እንደምትፈልግ ገልጸዋል፤ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣሉ ማናቸውንም የመርከብ ማለፊያ ክፍያዎችንም አሜሪካ እንደማትፈቅድ ተናግረዋል።
በአንጻሩ የኢራኑ ከፍተኛ መሪ አያቶላ ሙጅተባ ኻሜኒ የዳበረው ዩራኒየም በማንኛውም ሁኔታ ከሀገር መውጣት እንደሌለበት ተናግረዋል።
የሁለቱ ወገኖች አቋም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ባለው የሰላም ድርድር ላይ ትልቁና እልባት ያላገኘው አጀንዳ ኾኖ በመቀጠል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶታል።
የሁለቱን ሀገራት ውጥረት ለማርገብ ከመሀል ኾና እየሰራች ያለችው ፓኪስታን ዛሬም ጥረቷን ቀጥላለች። ጦር አዛዧ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒርም ቴህራን ገብተዋል። በኢራን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እስካንደር ሞሜኒ አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢራን ኢንተርናሽናል ዘግቧል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
