
ከሚሴ: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባቲ ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።
የባቲ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሰይድ አሕመድ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል ብለዋል።
ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክት፣ መንገድ፣ ድልድይ እና ትምህርት ቤት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ የመስኖ ፕሮጀክቱ ከ200 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ400 በላይ አባዎራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
የተገነባው መንገድ የአካባቢውን ምርት ለገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች የማኅበረሰቡን የልማት ጥያቄ የሚያቃልሉ መኾኑን አስረድተዋል።
በተለይ አካባቢው በአትክልት እና ፍራፍሬ የሚታወቅ በመኾኑ በአካባቢው የሚመረቱ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ፕሮጀክቶች መኾናቸውንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ይማም ኢብራሒም
#አሚኮ_ዜና #የመሠረተልማት_ግንባታ #ባቲ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
