🗳️ 10 ቀናት ብቻ በቀሩት ምርጫ የሚበጅዎትን ለመምረጥ ምን ያህል ተዘጋጅተዋል ?

29

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 🇪🇹 ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ ካርድ አውጥቶ የምርጫውን ቀን እየተጠባበቀ ይገኛል። የምሥራቅ በለሳ ወረዳ ነዋሪዎችም የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ።

አሚኮ ያነጋገራቸው የወረዳው ነዋሪዎች ቀደም ብለው የምርጫ ካርድ ወስደዋል። በተለያየ ጊዜ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው ለምርጫው በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

በምርጫው ዕለትም የሚበጃቸውን ተወካይ በያዙት ካርድ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።

ሌላኛዋ የወረዳው ነዋሪ በሰጡት አስተያየት ምርጫው በዋናነት የሚጠቅመው ሕዝቡን ነው ብለዋል። በምርጫው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ሀሳባቸውን አጋርተውናል።

በተለይም ሴቶች እኩልነታቸውን የሚያረጋግጡበት አጋጣሚ በመኾኑ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

የወረዳው ነዋሪዎች የምርጫ ካርዳቸውን በእጃቸው በማስገባት የታሪክ አሻራቸውን ለማሳረፍ መዘጋጀታቸው በሕዝቡ ዘንድ ያለውን የግንዛቤ ደረጃ እና የዴሞክራሲ ፍላጎት በግልጽ የሚጠቁም ነው።

🕊️ ሁሉም ዜጋ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመኾን ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ልማት ኀላፊነቱን ይወጣ ዘንድ የነዋሪዎቹ መልዕክት ነው።

“እርስዎስ የሚበጅዎትን ለመምረጥ ምን ያህል ተዘጋጅተዋል”?

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

#አሚኮ #ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !.

Previous article“ብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ፖሊሲዎችን ዘርግቶ ሀገርን ለማሻገር እየሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleበባቲ ወረዳ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።