🗳️ “ሴቶች በድምጻቸው ሀገር ይገነባሉ ፤ በአንደበታቸው ሰላምን ይሰብካሉ”

22

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ማኅበራዊ ዘርፍ ሥር የሚገኙ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የጋራ ውይይት አካሂደዋል።
​
​የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኅላፊ ዝና ጌታቸው ባለፉት አምስት ዓመታት ሴቶችን በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ ያደረጉ ትልልቅ የለውጥ ሥራዎች ሢሠሩ ቆይተዋል ብለዋል።

​ሴቶችም ጥቅማቸውን ለማስቀጠል የምርጫ ካርዳቸውን በመያዝ ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ በነጻነት እና በንቁ ተሳትፎ ለመምረጥ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ እንዲኾን ሴቶች የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

​የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኅላፊ ኢየሩስ መንግሥቱ ሴቶች የማኅበረሰቡ ግማሽ አካል በመኾናቸው ተሳትፏቸው ወሳኝ ነው ብለዋል።

​ባለፉት ጊዜያት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ዘርፎች ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ በርካታ አካታች ሥራዎች የተሠሩ ስለመኾኑም አንስተዋል።

የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኅላፊ ባንቻምላክ ገብረ ማርያም ምርጫው ሕጋዊ የመንግሥት ሥርዓት ለመገንባት እና በጥበብ የሀገርን ሰላም ለማጽናት ወሳኝ ምዕራፍ መኾኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሠራው ሥራ በተግባር የታዩ ለውጦች ተመዝግበዋል ነው ያሉት። በፖለቲካው ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሀገርን ወክለው ውሳኔ እስከማሳለፍም ደርሰዋል ብለዋል ኀላፊዋ።

​ሴቶች የተገኙትን ዕድሎች በአግባቡ መጠቀም እንደሚኖርባቸውም አንስተዋል።

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

#አሚኮ #ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleምርምር እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣይ የሚዲያዎች ትኩረቶች መኾን ይገባቸዋል።
Next article“ብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ፖሊሲዎችን ዘርግቶ ሀገርን ለማሻገር እየሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ