
አዲስ አበባ: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ ሠብሣቢ እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መገናኛ ብዙኃን ራሳቸውን አኹን ባለው የቴክኖሎጅ አቅም ልክ መገንባት እና ማዘመን አለባቸው ብለዋል።
አምባሳደር ሬድዋን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያን በጎበኙበት ወቅት አንደገለጹት ሚዲያዎቹ በዲጂታል ዘመን ልክ ኾኖ ለመገኘት ያከናወኗቸው ተግባራት የሚበረታቱ መኾናቸውን አንስተዋል።
ምርምር እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣይ የመገናኛ ብዙኅን ትኩረት መኾን እንዳለባቸው አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ በጉብኝታችን ሁለቱ ተቋማት ለዲጂታል ዘርፉ የሰጡትን ትኩረት ተመልክተናል፣ ሌሎች መገናኛ ብዙኃንም የዲጂታል ቴክኖሎጅ መሠረተ ልማት በመገንባት ሀገራዊ አጀንዳዎችን ተደራሽ ማድረግ ይገባቸዋልም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙኀን ልምድ በመለዋወጥ ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘጋቢ- ኤልሳ ጉዑሽ
#አሚኮ_ዜና #መገናኛ_ብዙኅን #ለዲጅታል_ዘርፍ #ግንባታ #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
