
ገንዳውኃ: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ “በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ መልዕክት ወጣቶች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እያሱ ይላቅ ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን እየሠራን ነው ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ያለ ወጣቶች ተሳትፎ ለውጥ ሊመጣ ስለማይችል ወጣቶችን በማሳተፍ ሀገሪቱን ወደ ተሻለች ሀገር ማሸጋገር ያስፈልጋል ነው ያሉት። ምርጫ የሥልጡን ሕዝብ መገለጫ መኾኑንም ተናግረዋል።
ወጣቶች ከመምረጥ ባሻገር የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በሰልፉ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማሥተባባሪያ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ጌጡ ብልጽግናን መምረጥ ሰላም እንዲሰፍን፣ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ እንድታድግ ማድረግ፣ የነገዋን ዘመናዊት ኢትዮጵያ እና የወጣቶችን ብሩህ ተስፋ ማረጋገጥ ነው ብለዋል።
ብልጽግና ለወጣቶች የሥራ ዕድልን የሚፈጥር እና ምቹ ሁኔታን የሚያመቻች ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል።
ፓርቲው ሰው ተኮር የልማት ተግባራትን እና ለከተሞች አዲስ ገጽታን እና ለዜጎች ደግሞ ምቹ ከባቢን እየፈጠረ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አብዱልከሪም ሙሐመድ ወጣቶች ለሀገር ሰላም፣ ልማት እና ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መኾኑን ተናግረዋል።
ወጣቶች በአንድነት እና በጠንካራ ተሳትፎ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚችሉም ገልጸዋል።
ምርጫ የሕልውና ጉዳይ መኾኑን ወጣቶች በመረዳት ይኾነኛል፣ ያስተዳድረኛል እና ይመራኛል የሚሉትን ፓርቲ መምረጥ አለባቸው ብለዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት የነገዋን ታላቅ ኢትዮጵያ ለመገንባት መነሻዎች መኾናቸውን ወጣቶች በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።
ምርጫው ሰላማዊ በኾነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ምዕራብ_ጎንደር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
