
ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ደቡብ ወሎ በግብርና የልማት አብዮት ላይ ነው ብለዋል።
የሐይቅ ዙሪያ አርሷደሮች መሬት እና እርሻቸውን ከጫት ወደ ሙዝ ኩታገጠም አሸጋግረው በአዲስ የልማት ግስጋሴ ላይ መኾናቸውን ገልጸዋል። አርሷደሮቹ የአካባቢን አንጻራዊ የልማት ጉልበት መለየት እና ወደ አትራፊ እና ዘላቂ የግብርና ጎዳና መሸጋገር ይገባል የሚለውን ሀገራዊ መርህ እና ስምሪት ተግብረው አሳይተዋል ነው ያሉት።
በዞኑ የለጋምቦ እና የመቅደላ ወረዳ አርሷደሮች በስንዴ ልማት አብዮት የእርሻ ከባቢያቸውን የስንዴ ስጋጃ እያለበሱ መኾናቸውን አንስተዋል።
ይህ የልማት ትጋት ኢትዮጵያ ለጀመረችው ለምግብ ሉዓላዊነት የጨከነ እቅድ እና ተግባር ተደማሪ ጥሪት እና ወረት ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
