የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንዳንድ ቃላት ትርጓሜ

7

 

👉 “ቦርድ” ማለት በዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 መልሶ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡

👉 “ምርጫ” ማለት በፌዴራል እና በክልል ሕገ መንግሥታት እንዲሁም በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት የሚካሄድ የጠቅላላ፣ የአካባቢ፣ የማሟያ ወይም የድጋሚ ምርጫ ነው፡፡

👉 “ጠቅላላ ምርጫ” ማለት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡

👉 “የአካባቢ ምርጫ” ማለት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የሚካሄድ የብሔረሰብ ዞን፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡

👉 “ማሟያ ምርጫ” ማለት በመራጮች ውሳኔ ከምክር ቤት መነሳትን ጨምሮ በማንኛውም ምክንያት በየደረጃው የሚገኙ የተጓደሉ የምክር ቤት አባላት መቀመጫዎችን ለመሙላት የሚካሄድ ምርጫ ነው፡፡

👉 “ድጋሚ ምርጫ” ማለት በዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7(16) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ቦርዱ የምርጫ ውጤቱ እንዲሰረዝ ሲወስን፤ በዚህ ዐዋጅ አንቀጽ 154 መሠረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ሲወስን፤ ወይም ዕጩ ተወዳዳሪዎች እኩል ድምጽ በማግኘታቸው ምክንያት አሸናፊውን ለመለየት የሚካሄድ ምርጫ ነው፡፡

👉 “ሕዝበ ውሣኔ” ማለት በኤ.ፌ.ደ.ሪ ሕገ መንግሥት ወይም አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ሲወሰን የሕዝብ ፍላጎት ለመለካት ወይም የሕዝብን ውሳኔ ለማወቅ የሚደረግ የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ነው፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Previous articleብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችን የሀገር ግንባታ ዋና ተዋናይ አድርጎ እየሠራ ነው።
Next article“ደቡብ ወሎ በግብርና የልማት አብዮት ላይ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ