ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችን የሀገር ግንባታ ዋና ተዋናይ አድርጎ እየሠራ ነው።

3

 

ጎንደር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክል ድንጋይ ከተማ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ የወጣቶች ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል።

የድጋፍ ሰልፉ “በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መልዕክት ነው የተካሄደው ።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ ወጣቶች አዲስ ሐሳብን የሚያፈልቁ ለሀገር አለኝታ በመኾናቸው ብልጽግና ፓርቲ ዋና ተዋናይ አድርጎ እንደሚመለከታቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለመቀየር በሚደረገው ሂደት ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በክህሎት ማሳደግ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

ወጣቶች በፖለቲካው መስክ ሐሳባቸው እንዲደመጥ ብልጽግና እየሠራ መኾኑን የገለጹት ኀላፊዋ ወጣቶች ሐሳብን በሐሳብ የማሸነፍ ልምምድ ውስጥ እንዲገቡ ፓርቲው አዲስ የውይይት ባሕል ተግባራዊ እያደረገ ነው ብለዋል።

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አስረሳው ደሴ ፓርቲው ማንነት እንዲከበር፣ እኩልነት እንዲሰፍን እና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲከበር ዕድል የሰጠ መኾኑንም አብራርተዋል።

ወጣቶች በሰባተኛው ጠቅላላ እና የክልል ምክር ቤት የቀረቡ እጩዎችን እንዲመርጡም ጠይቀዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የአካባቢውን ሕዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እየሠጠ ያለ ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ እና አሳታፊ እንዲኾን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ለአሚኮ ሀሳባቸው የሰጡ የሰልፉ ተሳታፊዎች አሳውቀዋል።

ዘጋቢ፦ተስፋየ አይጠገብ

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ላይ_አርማጭሆ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“መገናኛ ብዙኅን በምርጫ ሥራዎች ላይ በገለልተኝነት መሥራት ይገባቸዋል” ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንዳንድ ቃላት ትርጓሜ