🗳️ ምርጫ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማደጊያ ዕድል ነው።

3

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ሴቶችን ወደ ፖለቲካው መድረክ እና ወደ መሪነት ለማምጣት አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

በርካታ ሴቶች ከፌዴራል እስከ ታችኛው ተዋረድ ድረስ የመንግሥት ተቋማትን እየመሩ ይገኛሉ።

🗳️ ምርጫ ደግሞ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ወደ መሪነት ለማምጣት አንዱ መንገድ ነው።

በባሕር ዳር ከተማ ያነጋገርናቸው ሴት ነዋሪዎችም በምርጫ ሂደቱ ሴቶች በንቃት እየተሳተፉ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ወጣት እመቤት ተበጀ የከተማ አሥተዳደሩ ሴቶች በምርጫ ሂደቱ ካርድ በማውጣት፣ በማስወጣት እና ቅስቀሳ በማድረግ ከወንዶች ዕኩል ተሳትፎ እያደረጉ ነው ብላለች።

🕊️ ሴቶች ሰላም ፈላጊ መኾናቸውን የምታነሳው ወጣቷ ምርጫው ሴቶች ወደ መሪነት መጥተው ለሀገር ሰላም እንዲሠሩ ዕድል ይፈጥራል ነው ያለችው።

በፌዴራልም ኾነ በክልል ምክር ቤቶች ለሴቶች መብት መከበር የሚታገሉ ሴት ተወካዮቻችንን ለመምረጥ እና የሴቶችን ችግር የሚፈቱ ሴት መሪዎችን ወደ ፊት ለማምጣት ዕድል እንደሚሰጥ ገልጻለች።

ሌላኛዋ ነዋሪ ሰናይት ጸጋዬ ሴቷ ወደ አደባባይ ወጥታ መብቷን እንድታስከብር፣ ለሴቷ ጥብቅና እንድትቆም እና ሥልጣን ይዛ በሀገሯ ጉዳይ እንድትወስን ያስችላታል ብላለች። ካርድ ያወጣችው እና ለመምረጥ የተዘጋጀችውም ይህን ተገንዝባ እንደኾነም ገልጻለች።

ነዋሪዎቹ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ላይ ሴቶች ለአካታችነት ትኩረት ይሰጣል፤ ለሴቶች መብት መከበር ይሠራል የሚሉትን ፓርቲ የሚመርጡበት ቀን መኾን አለበትም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ

#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleኢትዮጵያ ትናንትናን እና ዛሬን አክማ ነገን ለመሥራት ርብርብ እያደረገች ነው።
Next articleሴቶች ተጠቃሚነታቸውን በምርጫ ካርዳቸው ይወስናሉ!