“ብልጽግና ሴቶች እና ወጣቶች አቅማቸውን እንዲጠቀሙ አድርጓል” የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታይቱ ካሴ

7
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የሴቶች እና የወጣቶች የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።
በሰልፉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በሰቆጣ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ፋንታይቱ ካሴ ብልጽግና ፓርቲ በወንድማማችነት እና በኅብረ ብሔራዊነት የተገነባሽ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው።
ብልጽግና የሴቶችን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን የገለጹት አፈጉባኤዋ ፤ ሴቶች በሀገራቸው ጉዳይ ግንባር ቀደም ሆነው እንዲሠሩ እና ሕዝባቸውን እንዲወክሉ ሰፊ ዕድልን የፈጠረ ፓርቲ መሆኑንም አብራርተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሴቶችና ወጣቶች አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ዕድል የከፈተ የወጣቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ሀገርን መረከብ አለበት ብሎ የሚያምን ፓርቲ ነውም ብለዋል ።
ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሳካት ዋናው ባለቤት ወጣቱ ነው ያሉት አፈጉባኤ ፋንታይቱ ፤ የነገዋን ተምሳሌት ኢትዮጵያ ለመገንባት ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተሳታፊዎቹ በሀገራዊ አንድነት፣ በሰላም ግንባታ፣ በሴቶች ተሳትፎ እና በልማት ሂደቶች ዙሪያ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የብልጽግና ፓርቲን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፉ ገልፀዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleድምጽ ከመስጠት ባሻገር ለምርጫው ሰላማዊነት በጋራ መሥራት ይገባል።
Next articleሰላም የሚረጋገጠው በሁሉም አዎንታዊ ተሳትፎ ነው።