ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ለምርጫው ሰላማዊነት በጋራ መሥራት ይገባል።

6
እንጅባራ: ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊ ሴቶች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ በጎዳና ላይ ሰልፍ ገልጸዋል።
የድጋፍ ሰልፉ “በፀና እና በተደራጀ የሴቶች ድምጽ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት ነው የተካሄደው።
ሰልፈኞቹ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል።
በፓርቲው መሪነት የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ከግብ እንዲደርሱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድጋፋቸውን ለመስጠት ዝግጁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ለምርጫው ሰላማዊነት በጋራ መሥራት እንደሚገባም ሰልፈኞቹ ገልጸዋል። ለዚህም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ ብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ድል እየቀየረ የሀገሪቱን የዕድገት ጉዞ እያፋጠነ ያለ አሻጋሪ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል።
ፓርቲው የሀገሪቱን ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ዕቅዶች እንዳሉት ያነሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሴቶች ለዕቅዶቹ ተፈፃሚነት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ በመስጠት አጋርነታቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን ሰላም ለማጽናት የሚያስችል ወሳኝ ምዕራፍ መኾኑንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየሴቶችን አቅም መገንባት ሀገርን ማሻገር ነው።
Next article“ብልጽግና ሴቶች እና ወጣቶች አቅማቸውን እንዲጠቀሙ አድርጓል” የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታይቱ ካሴ