ሴቶችን በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ማሳተፍ ለሀገር እድገት ወሳኝ ነው።

6
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በላይ አርማጭኾ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች መጭው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ያለመ የድጋፍ ሰልፍ አካሄደዋል። በትክል ድንጋይ ከተማ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፉ የወረዳው ሴቶችና የመንግሥት ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ ብልጽግና ፓርቲ
ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ አበክሮ እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ሴቶችን በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ማሳተፍ ለሀገር እድገት ወሳኝ ስለመኾኑም ጠቁመዋል። ሴቶች ሰርተው እንዲለወጡ እና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ ፓርቲያቸው በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ አስረሳው ደሴ ብልጽግና ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሠራ ያለ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል።
የጋራ ሀገር የኾነችውን ኢትዮጵያን ለመገንባትና ለማስቀጠልም ፓርቲው እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleባንኩ ዘላቂ የማኅበረሰብ ልማትን ለማረጋገጥ እየሠራ ነው።
Next articleምርጫው ለነገ መሠረት የምንጥልበት ነው።