ባንኩ ዘላቂ የማኅበረሰብ ልማትን ለማረጋገጥ እየሠራ ነው።

4
አዲስ አበባ: ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አቢሲኒያ ባንክ የ5ኛ ዙር “እችላለሁ እኔ” እና የ2ኛ ዙር “ይጀምሩ ያድሱ” የሽያጭ ዘመቻ የሽልማት መርሐግብሩን አካሂዷል።
የአቢሲኒያ ባንክ ችፍ ኢንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር መሠረት አስፋው መርሐግብሩ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን መሠረት አድርጎ በየዓመቱ የሚከናወን መኾኑን አንስተዋል።
በአምስተኛው ዙር አሸናፊ የኾኑ እድለኞችንም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል::
ባንኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም፣ የፋይናንስ አካታችነት እና ዘላቂ የማኅበረሰብ ልማትን ለማረጋገጥ ያለውን ጽኑ አቋም በተግባር ማሳየቱን ተናግረዋል።
በመርሐ ግብሩ በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን ሞት ለመቀነስ የ3 ቀናት ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ ዘመቻም ተካሂዷል ነው ያሉት።
በተጨማሪም ከ550 በላይ ለሚኾኑ ሴት ነጋዴዎች ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና የገበያ ትሥሥር እንዲፈጥሩ ተደርጓልም ብለዋል።
ከሁለት ሚሊዮን በላይ የዕጣ ተወዳዳሪዎች በነበሩበት “እችላለሁ እኔ” የሽልማት መርሐግብርም በአንደኛ ዕጣ የመኪና ሽልማት አበርክቷል።
ዘጋቢ፦ቴዎድሮስ ኀይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ችግርን የተቋቋመ፣ በተግባር የተፈተነ”
Next articleሴቶችን በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ማሳተፍ ለሀገር እድገት ወሳኝ ነው።