
ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
በአሥተዳደር ዘርፍ የመንግሥት ሠራተኞች መድረክ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ልዩ አማካሪ ይትባረክ አወቀ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ስኬታማ እንዲኾን አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።
ለስኬታማነቱም የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑን አንስተዋል። የመንግሥት ሠራተኞችም ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በተግባር የተፈተነ፤ የገጠሙትን ችግሮች ተቋቁሞ ሀገር እና ሕዝብ ለማሻገር በትጋት እየሠራ ያለ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል።
በገጠር ዘርፍ የመንግሥት ሠራተኞች መድረክ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የሚያሻግር እና ለትውልድ የሚተርፍ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ እንደኾነ ገልጸዋል።
ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና ሀገር የሚያሻግር ትውልድ እንዲፈጠር የጠራ ፖሊሲ ቀርጾ እየሠራ ስለመኾኑም አብራርተዋል።
በክልሉ ያሉት ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ እና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ፓርቲው በቁርጠኝነት እየሠራ ስለመኾኑም በመድረኮቹ መልእክት ተላልፏል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
