በዞኑ ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን እየተሠራ ነው።

4

 

ደብረማርቆስ: ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱ ጉዳዮች መካከል ምርጫ አንዱ ነው፡፡

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ሰላም እና የዴሞክራሲ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ እንደኾነም ይታመናል፡፡ ለዚህ ምርጫ መሳካትም መንግሥት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ግርማ ጫኔ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ መልኩ እንዲከናወን አጠቃላይ የጸጥታ ኀይሉን በማቀናጀት በምርጫ ሥነ-ምግባር ደንቡ ላይ ሥልጠና ከመስጠት ጀምሮ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዞኑ ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን ኅብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ስለመከናወናቸውም አብራርተዋል፡፡

ዜጎች ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ እንዲመርጡ እና ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት ኀላፊው ለምርጫው ስኬታማነት ዜጎች ለጸጥታ ኀይሉ ተባባሪ እንዲኾኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱንም የሚያደናቅፉ ሁኔታዎችን ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ኅብረተሰቡ ኀላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ምሥራቅ_ጎጃምዞን #አማራክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ የፒዮንግያንግ ጉዞ እና የቤጂንግ ዲፕሎማሲያዊ ሚና።
Next article“በድምፅ መምረጥ እና ሰላምን ማጽናት ለነገ የማይተው ኅላፊነቶች ናቸው” አቶ አሰፋ ጥላሁን