የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ የፒዮንግያንግ ጉዞ እና የቤጂንግ ዲፕሎማሲያዊ ሚና።

6
ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ በዶናልድ ትራምፕ እና በኪም ጆንግ-ኡን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማደስ በሚቀጥለው ሰኞ ወደ ሰሜን ኮሪያ ሊጓዙ እንደሚችሉ ቴሌግራፍ የዜና አውታር ዘገበ።
ጉብኝቱ በትራምፕ እና በኪም መካከል የተቋረጠውን ግንኙነት እንደገና ያነቃቃል የሚል ከፍተኛ ተስፋን ጭሯል።
የደቡብ ኮሪያው ዮንሃፕ የዜና ወኪል ፕሬዝዳንት ዢ በቅርቡ ፒዮንግያንግን እንደሚጎበኙ የስለላ መረጃዎችን ጠቅሶ አስነብቧል። የውስጥ ምንጮች እንደሚጠቁሙት የቻይናው መሪ በሁለቱ ወገኖች መካከል ዋነኛ አስታራቂ ኾነው ያገለግላሉ።
ትራምፕ እና ኪም ከመጀመሪያው የትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ዘመን ወዲህ አልፎ አልፎ የሚታይ ግንኙነት ነው የነበራቸው።
ዋይት ሀውስ እንደገለጸው ሁለቱ መሪዎች ሰሜን ኮሪያ ከኑክሌር ነጻ መኾን አለባት በሚለው አጀንዳ ላይ ተስማምተዋል።
በነሐሴ 2025 ትራምፕ የሰሜን ኮሪያውን አምባገነን መሪ እንደሚረዷቸው እና ከእሳቸው ጋር በጣም በጥሩ ሁኔታ እንደሚግባቡ በመግለጽ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ሊያገኟቸው እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር።
ትራምፕ እ.ኤ.አ. በ2019 በሥልጣን ላይ እያሉ የሰሜን ኮሪያን ምድር የረገጡ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው።
ፕሬዝዳንት ዢ ራሳቸው ሰሜን ኮሪያን ለመጨረሻ ጊዜ የጎበኙት ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት በሰኔ 2019 ዓ.ም ነበር። ያ ጉብኝት ከ14 ዓመታት በኋላ የአንድ የቻይና መሪ የመጀመሪያው ይፋዊ የሀገር ጉብኝት ነበረ።
ፑቲን እና ዢ የወታደራዊ እና የህዋ ትብብርን ጨምሮ ከ20 በላይ ስምምነቶችን መፈረማቸውን ቴሌግራፍ ጠቁሟል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleሴቶች የሀገር መሠረቶች ናቸው!
Next articleበዞኑ ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን እየተሠራ ነው።