
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን፣ የፋርጣ ወረዳ እና የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ሴት የመንግሥት ሠራተኞች 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የአደባባይ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮነን የዛሬውን የድጋፍ ሰልፍ ለየት የሚያደርገ የጥንካሬ ተምሳሌት በሆነችው እትጌ ጣይቱ አደባባይ መሆኑ ነው ብለዋል።
ብልጽግና የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሠራ እና የሚያጠናክር አካታች ፓርቲ መሆኑን በድጋፋ ሰልፉ ላይ ማየት ተችሏል ብለዋል።
ሴቶች ተሳትፏቸውን በማሳደግ ግንቦት 24 የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በመኾነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ (ዶ.ር) እንዳሉት ከለውጡ መንግሥት ወዲህ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ በመሆኑ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተሻለ መንገድ እንዲከናወን ሴቶች የሚያሳዩት ከፍተኛ ተሳትፎ ይበል የሚያሰኝ ነውም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
