
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት እና ደጋፊዎች “በጸና እና በተደራጀ የሴቶች ድምጽ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እናሻግራለን!” በሚል መሪ ቃል የፓርቲያቸውን የጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ በድምቀት እያካሄዱ ነዉ።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያመጣቸውን ሁለንተናዊ ስኬቶች በተለይም የሴቶችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራትን በአደባባይ ሰልፉ አንስተዋል።
ሴቶች ፓርቲው የጀመራቸውን የልማት እና የሰላም ጉዞዎች ከዳር ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹ ሲኾን፤ በቀጣይም ለፓርቲው ስኬትና ለሀገር ግንባታ የጀመሩትን የተደራጀ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
