
በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ነዋሪዎችም “የምርጫ ካርድ በእጃችን ነው፤ መምረጥም መብታችን ነው” በሚል እሳቤ ለምርጫው ዝግጁ መኾናቸውን ነግረውናል።
በያዙት የምርጫ ካርድ የፈለጉትን የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት መምረጥ የማንኛውም ዜጋ መብት መኾኑን ገልጸዋል።
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጓቸውን የምርጫ ክርክሮች በንቃት እና በትኩረት እየተከታተሉ መኾናቸውንም አንስተዋል።
ሀገር ሰላም ስትኾን ሁሉም ነገር መልካም እንደሚኾን የገለጹት ነዋሪዎቹ ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ኀላፊነታችን እንወጣለን ብለዋል።
በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ማኅበረሰቡ የራሱን አካባቢ በንቃት ከመጠበቅ ባለፈ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ሀገር የሰጠችንን የዜግነት አደራ በዕለቱ ድምጻችንን በአግባቡ በመስጠት መወጣት ይኖርብናል ነው
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
