
ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ቅስቀሳ አድርገዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ወረዳው በአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም በሌሎች የሰብል ልማቶች ውጤታማ እየኾነ መምጣቱን ተናግረዋል።
ብልጽግና የቃሉ ወረዳ ሕዝብን የመስኖ፣ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ ጥያቄ በተግባር ምላሽ ሰጥቷል ብለዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የመስኖ ልማትን በባሕላዊ እና በዘመናዊ መንገድ በሙሉ አቅም መጠቀም ግብርናን ለማዘመን ወሳኝ መኾኑን ተናግረዋል።
ብልጽግና ቃል የገባውን በተግባር የሚፈጽም ፓርቲ እንደኾነም ገልጸዋል። ማኅበረሰቡ ሰላምን በማጽናት ይበልጥ የልማት ተጠቃሚ ለመኾን የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
