“ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች ሳይበገር ታሪክ እየሠራ ይቀጥላል” አቶ ሲሳይ ዳምጤ

5
ደብረ ታቦር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለአርሶ አደሮች የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኅላፊ ሲሳይ ዳምጤ ብልጽግና ፓርቲ በመልካም አሥተዳደር እና በሌሎች ዘርፎች ድል እያስመዘገበ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል። ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች ሳይበገር ታሪክ እየሠራ ይቀጥላል ነው ያሉት።
የአርሶ አደሮችን የምግብ ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባለፈ የስንዴ ምርትን ለውጭ ሀገራት የመላክ ግብን ይዞ እየሠራ እንደኾነም ገልጸዋል።
የፋርጣ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ጌትነት ኢትዮጵያን ከበለጸጉ ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እየታተረ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል። አርሶ አደሮች መጻኢ ዕድላቸው በእጃቸው የያዙት የምርጫ ካርድ እንደኾነ ነው የገለጹት።
የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አማረ ይሁኔ ብልጽግና ፓርቲ የሚታዩ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።
በዘላቂነት የአርሶ አደሮችን ቁልፍ ጥያቄ ለመፍታት በሀገር ውስጥ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማምረት ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleሰላምን ከማረጋገጥ በተጓዳኝ ልማቶች እየተሳለጡ ነው።
Next article“ብልጽግና ቃል የገባውን በተግባር የሚፈጽም ፓርቲ ነው” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)