
ደሴ: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ብዙ የመልማት ጸጋ ያላት ናት፤ ፓርቲውም የታሪክ ስብራቶችን በመጠገን በኹሉም ዘርፍ ስኬታማ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በጤና፣ በትምህርት እና በግብርናው ዘርፍ በርካታ የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
የምንፈልጋትን እና የምንመኛትን የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በፈተና ውስጥም ኾኖ የሠራ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ብልጽግና ዕውነትን፣ ዕውቀትን እና ጥበብን ተጠቅሞ የሚሠራ ፓርቲ መኾኑን ገልጸዋል። በመንግሥት እና በሕዝብ ትብብር በተከናወኑ ሥራዎች ፓርቲው አመርቂ ውጤት ማስገኘቱን አንስተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኘው የብልጽግና ፓርቲ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር በርካታ የልማት ሥራዎችን የተገበረ ፓርቲ መኾኑን አመላክተዋል።
የመደመር እሳቤ የኾነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ ሀገራችን ወደ ተምሳሌት ሀገር ትሻገር ዘንድ የበኩላችሁን ተወጡ ብለዋል።
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
