ቻይና እና ሩስያ ለዓለም ሰላም በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ።

4

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቤጂንግ የሁለትዮሽ ውይይት እያካሄዱ ነው። መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት፣ በንግድ፣ በአሜሪካ፣ እስራኤል-ኢራን ጦርነት እና በዩክሬን ግጭት ዙሪያ እየመከሩ ነው።

የዩክሬን ጦርነት አምስተኛ ዓመቱ ላይ በመድረሱ ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምታደርገው የጋዝ ሽያጭ ቀንሷል። በመኾኑም ሞስኮ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከቻይና ጋር ያለውን የኢነርጂ ትብብር ማጠናከር ትሻለች።

ለዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የኢነርጂ ስምምነት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ሁለቱ መሪዎች በሉዓላዊነት እና በብሔራዊ አንድነት ጉዳዮች ላይ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ ዝግጁ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን የሀገራቱ ትስስር በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ የማረጋጋት ሚና እየተጫወተ መኾኑን ገልጸዋል። ከማንም ወገን ሳይሰለፉ ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና በጋራ እንደሚሠሩም ማረጋገጣቸውን የቻይና የመንግሥት መገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ ሌሎች ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዘጋቢ፦ስማቸው አጥናፍ

#አሚኮ_ዜና #የሩስያ_ቻይና #ጥምረት #ለዓለም_ሰላም

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል የእናቶች እና የሕጻናት ሕክምና ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።