“ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶች ተጠቃሚነት የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ ነው” አቶ እንድሪስ አብዱ

5

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አሥተባባሪነት ”በጸና እና በተደራጀ የሴቶች ድምጽ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እናሻግራለን” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች የድጋፍ ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶች ተጠቃሚነት የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ሴቶችን በኹሉም ዘርፍ ተሳታፊ ለማድረግ እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ ሴቶችን በአመራር ደረጃም ተሳታፊ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል። ይህ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ሴቶችን በማደራጀት በኹሉም የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲኾኑ ፓርቲው በትኩረት እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ሴቶች ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የከተማው ሴት የብልጽግና ደጋፊዎች እና አባላትም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ከሚሴ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየሚሊሻ 30ኛ የምሥረታ በዓል በሁመራ ከተማ እየተከበረ ነው።
Next articleየከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል የእናቶች እና የሕጻናት ሕክምና ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።