በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ ጠንካራ እና የተቀናጀ እርምጃ መወሰዱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ክፍለ ጦሮች አስታወቁ።

7
ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጽንፈኛው ላይ ከባድ ምት በማሳረፍ ሕግ እያስከበሩ መኾኑን ክፍለ ጦሮች አስታውቀዋል።
የስድስተኛ ዕዝ ወልወል ክፍለ ጦር በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ዘይት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰዱ ተገልጿል። በበርካታ ጠላትት ላይ እርምጃ በመውሰድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን እና ተተኳሾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አለምሰገድ ተስፋዬ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ዞን ግዳጁን እየፈጸመ የሚገኘው የምሥራቅ ዕዝ አንድ ክፍለ ጦር በጽንፈኛ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ አራት ጽንፈኛው አመራር ብሎ የሚጠራቸውን ግለሰቦችን ጨምሮ በበርካቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
የክፍለ ጦሩ አዛዥ ሌትናል ኮሎኔል ምሥራቅ መንበር ክፍለ ጦሩ በሀሙሲት፣ በአንበሳሚ፣ በአርብ ገበያ፣ በምሥራቅ እስቴ እና አንዳ ቤት በተባሉ ቦታዎች በመግባት ጽንፈኛውን አሳዶ እየተቆጣጠረ መኾኑን ገልጸዋል።
አካባቢው ከነበረበት የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ በማድረግ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም አብራርተዋል። የተለያዩ መሳሪያዎችን እና ተተኳሾችንም በቁጥጥር ስር አውለዋል።
በተያያዘ በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተደራጀ ዘረፋ እና የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ በነበረው ጽንፈኛ ቡድን ላይ ጠንካራ እና የተቀናጀ እርምጃ መወሰዱን የኮር አዛዡ ኮሎኔል ገዳ በዳዳ ገልጸዋል።
መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየስፖርት ዘርፉን የቱሪዝም አቅም አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል።
Next articleበደቡብ ጎንደር ዞን እና በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ መሠረተ ልማቶች ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።