
አዲስ አበባ: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን “የስፖርት ቱሪዝም ለባሕል ልውውጥ እና ለሕዝብ ግንኙነት መጠናከር” በሚል መሪ መልዕክት የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቢኒያም ታዬ ስፖርት እና ቱሪዝም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች በመኾናቸው ይህንን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የሆቴል አና ቱሪዝም አማካሪው ሰለሞን ታዬ “ስፖርት የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ምንጭ በመኾኑ ዘርፉን የቱሪዝም አቅም አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል” ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ልማት ጥናት ኮሌጅ የመጡት ሽፈራው ሙለታ (ዶ.ር) በዓለም የቱሪዝም እንቅስቃሴ ውስጥ ስፖርት ቱሪዝም 10 በመቶ ያህሉን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከስፖርት ቱሪዝም አይነቶች በአትሌቲክስ ስፖርት ጎልታ የመውጣት ዕድል አላት ይህንን ማጉላት የምትችለዉ በተራራ ሩጫዎች ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የስፖርት ጋዜጠኛው ሰኢድ ኪያር የስፖርት ምልክት የኾኑ አትሌቶቻችን የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል ስያሜ መኾን እንደሚችሉ ተናግሯል።
በከተማዋ የተገነባው የስፖርት ፓርክ ኢትዮጵያ የስፖርተኞች መፍለቂያ መኾኗን በሚያሳይ መልኩ የተሠራ እንደኾነ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
