“ብልጽግና ቃል የገባውን በተግባር ፈጽሞ አሳይቷል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

6
ደሴ ፡ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገዋል።
የወረባቦ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አደም ሙሐመድ በወረዳው ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ መሠረተ ልማቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል። ይህም የማኅበረሰቡን የልማት ጥያቄ የፈታ መኾኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ልማት ላይ ዕድገትን ለማረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ዞኑ በስንዴ ልማት ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል። የፍራፍሬ ልማትን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በወረዳው በርካታ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋልና እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
“ልማት ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ስለማይኾን ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል” ብለዋል።
መንግሥት የአካባቢውን የልማት ሥራ ይበልጥ ለማጠናከር እየሠራ እንደኾነም ገልጸዋል። “ብልጽግና ለአካባቢው የገባውን ቃል መፈጸሙን በተግባር አይታችኋል” ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ልማትን፣ የሕዝብ ተጠቃሚነትን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ ቃል የገባውን በተግባር ፈጽሞ አሳይቷል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article
Next articleለ15 ሺህ ዜጎች አገልግሎት መስጠት የሚችል ጤና ጣቢያ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።