📺 🎙️ ሚዲያው የግብርና እና የእንስሳት ልማት ሥራዎችን ግንባር ቀደም አጀንዳ ሊያደርጋቸው ይገባል።

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ “የሚዲያ ሚና ለዘመናዊ ግብርና” በሚል መሪ መልዕክት ከሚዲያ እና ከኮሙኒኬሽን ተቋማት መሪዎች እና የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊዎች ጋር እየመከረ ነው።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ ዓባይ መንግሥቴ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ግብርናን ማዘመን ያስፈልጋል ብለዋል።

🇪🇹📈 የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ግብርናውን ማዘመን ወሳኝ መኾኑን አንስተዋል። ለዚህም በክልሉ በ25 ዓመቱ ዘላቂ የልማት ዕቅድ በግልጽ ተቀምጦ ወደ ተግባር ተገብቷል ነው ያሉት።

🚜🐄ሚዲያው ግብርና እና የእንስሳት ልማት ሥራዎችን ግንባር ቀደም አጀንዳ ሊያደርጋቸው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ይህንን መሠረት በማድረግ የግብርናውን አሠራር በሚዲያ እና በሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ ማስረጽ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ እንደገለጹት ግብርናውን ከኋላ ቀር አሠራር ወደ ዘመናዊ የግብርና አሠራር ሥርዓት ለማሸጋገር በትኩረት ተይዞ እየተሠራ ነው።

📈🌾 የግብርና ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም አሠራር፣ በመሥኖ ልማት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመጠቀም እና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል።

ለዚህ ሥራ ስኬታማነትም ከሚዲያዎች ጋር በቅርበት መሥራት እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የአሚኮ ጋዜጠኛ ደሳለኝ ክንዱ እንደገለጸው ሚዲያዎች በተለይም የግብርና ግብዓቶች ለአርሶ አደሮች እንዲዳርስ እና ግብርናው እንዲሳለጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው።

ለግብርናው መዘመን ሁሉንም አካላት አስተሳስሮ መረጃ በማዳረስ በኩል ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባቸውም አንስቷል።🎤

ዘጋቢ:-አሰፋ ልጥገበው

#አሚኮ #ግብርና #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

#አሚኮ_ዜና #ሚዲያ_ለግብርና #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤና ቢሮ ብቃት ያለው የሰው ኀይል ለመገንባት እየሠራ ነው።
Next article“በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም ቃል የገባነውን በተግባር አረጋግጠናል ” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር )